አንተ፣ ሰው አታዳምጥ፣
ትፈልጋለህ እንድትለወጥ
ከልብህ አዳምጥ ራስክንም ስማ
ጆሮህ አይሞላም ሁሉን ብሰማ
እስከተገኘህ በሂወት ጨዋታ፣
ነቃ ጠንቀቅ በል እንዳትረታ፣
እንደ እሳት ወላፈን ሁንባቸው፣
ሊያጠፉህ ሲያዳፍኑህ ለብልባቸው።
በየቀን በቀን ስራ ራስህላይ፣
ዋል ከታላቅጋር ከትንሽ ተለይ።
ደንበር እንዳለ ንቁ ወታደር፣
አላማህ ላይ እይ በጥሩ አተኩር።
እንዳትሸነፍ በሂወት ጨዋታ፣
በል ጠንከርከርከር ተበረታታ ።
ለደካሞች ቦታ የለም፣
ለጠንካሮች አድልታአለም።
አትረታ ጨዋታውን፣
እንዳታጣው ድሉን።
በዙሪያህ ላይ ያለ አዳኝ፣
ሲያሳድድህ እንደታዳኝ።
አምልጥና ሳትሆን ታዳኝ፣
ሁን አደኙን አዳኝ።
በዚህ ጨዋታ ሁን መሪንጉሥ፣
ባላ ጋራህን አፍርሰህ ደምስስ።
ሂወት ዝራና ልክ እንደ ፎኒክስ
ትቢያህን አራግፍ አመድ ላይ ተነስ፣
በፍጹም ፍፁም በጭራሽ ጭራሽ
ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ አትሽሽ
ሁን ልትገመት ማይገባ ሃይል
ለጠላቶችህ አስፈሪ ሀያል።
በዚህ ውስብስብ ሴረኞች ዓለም ፣
ከመጠንከር ውጭ ምርጫየለህም
አንፀባርቅ እንደ አልማዝ በደንብ አብራ፣
ጊዜህ ይሄው ነው ነው እና ያንተ ተራ
ግቦችህ ላይ አተኩር፣
በደንብ ጣር አነጣጥር
የሂወትን ውጊያ በጥሩተዋጋ፣
ለቀጣይ ምእራፍ ለመሻገር ጓጓ
ወደ ፊት መግፋቱን ቀጥልበት፣
የኋላንውን ወደ ኋላ ትተህለት
ውቅያኖስ ውስጥ በሚገኝ ስምጥ እንዳለ አሳ፣
በቀላሉም በካባዱም ማትታደን ሁን አበሳ፣
እየከፈትክ እይ ወደፊት መስኮት በሩን
አልፈህ አጥሩን ሂድእና ቃኝ ዓድማሱን
በኮንክሪት በታጠረ የፎቅ ጫካ ምንም የለም፣
ከሳጥን ውጭ ውጣ እና ሰብረህ አግኝ ሰላም
አትስጋ አዲስ ነገር ለመሞከር
በጀግንነት ተጓዝ ሀገር ለአገር
እወድቅ ይሆን ብለህ አትፍራ መውደቅን
ከውደክም ተማር ደግሞ መነሳትን
በዝግታም ቢሆን መራመድክን ቀጥል፣
ካሰብከው በመድረስ ትካሳለህ በድል።