( አድዋ )
--------------
የነጪ እንቢታን ገርስሶ፣
ቅኝ አገዛዝን አፍርሶ።
ለጥቁር ህዝቦች የበራ፣
መድፍ የታጠቀን ገጥሞ በካራ፣
ለነፃነቱ ሞት የማይፈራ፣
በጥቁርነቱ ኮርቶ ያኮራ፣
ስለ አድዋ ትንሽ እናውራ።
የስጋ የደም ያጥንት ግብር፣
ለታላቅ ሀገር ለነፃ ምድር፣
ጀግና ተዋድቋል በገደል በዱር።
ዋሽቸ እንደሆን ሮም ትመስክር፣
ሀበሻ ኩሩ የማይተነኩስ፣
ድንበር ተሻግሮ ነገር አይለኩስ፣
የማይወዳጅ ከሰይጣን ከርኩስ፣
የሰው ፈልጎ ጦር የማይደግስ፣
ከተነኮሱት እሳት ነው ትኩስ።
ጦር ሳይታጠቅ በክንዱ ብቻ፣
በራስ ጎበና በጀግናው በልቻ፣
ሁሉን ባልጠራ ብቻ ለብቻ፣
የሀገሬ ጀግና የለውም አቻ።
ላገሩ ኩራት ዘብ ለባንድራው፣
ርሀብ ጥማት የማይበግረው፣
ለጥቁር ህዝቦች ቀልጦ የበራው፣
ጀግና ጀብደኛ ሀበሻ ሙላው።
ክበሩ በብዙ የአድዋ ጀግኖች፣
ኮርተናል በናተ የልጃችሁ ልጆች።
አድዋ ጥልቅ ነው ታሪኩ ግዙፍ፣
እኔም ይችን ብየ ደከመኝ ልረፍ፣
አይቻል አባይን በማንኪያ መጪለፍ፣
ልሰናበታችሁ እያልኩ ዘራፍ ዘራፍ ዘራፍ።
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
ገጣሚ
ሁሴን ደረሰ
Hussen Ethiopia የካቲት 2013