በፍቅርሽ ተረትቸ በመውደድሽ
አሸነፈኝ ገላሽ ግሩም ለዛሽ
ደስታዬን የማገኘው በፈገግታሽ
የናፍቆት ሱሴ ጥሜ ሁኖ መአዛሽ
የፍቅር የመውደድ ጥጌ ነሽ
የማልተካሽ በምንም ለእኔ አንድ ነሽ
ነፍስን ዘርተሽ በልቤ ውስጥ
የዘመመውን ማንነቴን አርገሽው ቀጥ
የልቤን ምት ዝቅ ያለውን
ከፍ ያረግሽው አንች እኮ ነሽ
የዘወትር ልመናዬ የእኔ ፀሎት
የዘላለም ምኖቴ ነሽ የእኔ ህይወት
የአምላክ ተአምር አድሮ በእኛ መሀል
እንዲያኖረን አንድ አድርጎን ሳንለያይ
ጅምር ህልሜን ዳርቻውን በአይኔ እንዳይ
የተሰጠኝበረከትሽ እንዳይርቀኝ የእኔ ሲሳይ
እወድሻለሁ ፍፁሜ ነሽ
የፍቅር ቃል የማይገልፅሽ
የእኔ ልዩ የማፈቅርሽ
የእኔ ጣፋጭ የማፈቅርሽ