ዘፋኝ፦ ቃለአብ አመሰግናለው ለድጋፋቹ ሰኒ ነፂ በሶፊ እንዲዉም ላልጠራዋቹ ጓደኞቼ ትንሽ ትንሽ ብቻ (ወይም ትንሽን አልንቅም)
ትንሽ ተስፋ... ከመኖር እንዳልጠፋ
ትንሽ ትግስት... ሚያበረታኝ እስከንጋት
ሌሊቱ ረጅም ቢሆን፣ ጨለማው ቢከበኝ
ትንሽ ብርሃን በቂ ነው መንገዴን ለማየት
ትንሽ ጮራ... ጨለማውን እንዳልፈራ
ትንሽ ፅናት... በሽታዬን እንድችላት
ሕመም ቢከበኝ፣ ልቤ ቢደክመኝ
ትንሽ ጥንካሬ በቂ ነው እስትንፋሴን ለመቀጠል
ትንሽ ትንሽ ብቻ... የሚሆን ማበርቻ
ትንሽን አልንቅም... ከመኖር አልጠልቅም!
ተራራ ቢደራረብ፣ ባሕር ቢያገረሽብኝ
ትንሽ ተስፋ በቂ ነው ሕይወቴን ለማራመድ
ትንሽ ጉልበት... እንድወጣ ይሄን ዳገት
ትንሽ ሽንቁር... በቀዳዳዋ ለመብረር
ታስሬ ብሆን፣ ተይዤ ብቀር
ትንሽ ክፍተት በቂ ነው ነፃ ለመውጣት
ትንሽ አቅም... ከባድ ቀኔን እንድሸከም
ትንሽ ድጋፍ... ዝዬ እንዳልሸነፍ
ብቻዬን ብሆን፣ እጄ ባዶ ብትሆን
ትንሽ እገዛ በቂ ነው ወድቄ ላለመቅረት
ትንሽ ትንሽ ብቻ... የሚሆን ማበርቻ
ትንሽን አልንቅም... ከመኖር አልጠልቅም!
ተራራ ቢደራረብ፣ ባሕር ቢያገረሽብኝ
ትንሽ ተስፋ በቂ ነው ሕይወቴን ለማራመድ
ትንሽ ጥላ... በሀሩሩ እንዳልበላ
ትንሽ ምርኩዝ... ስዝል ለመመርኮዝ
ሲያቃጥለኝ ፀሐይ፣ ሲያንደረድረኝ ነፋስ
ትንሽ መጠጊያ በቂ ነው እስክትረጋ ሕይወት
ትንሽ ትንሽ ብቻ... የሚሆን ማበርቻ!
ትንሽን አልንቅም... ከመኖር አልጠልቅም!!
(ተደጋጋሚ)
ትንሽን አልንቅም... ከመኖር አልጠልቅም!!!
ትንሽ ተስፋ...
ትንሽ ትግስት...
ትንሽ ፅናት...
ከመኖር አልጠፋ... አልጠልቅም...