አንደ ሜሮን ቅባት ፣
በአናቴ ፈሰሽ ፣
ገነት እንድገባ ፤
በ ስምሽ ልጠመቅ ፣
ልቁረብ ፥ ንስሐ ልግባ ፤
አዲስ ህይወት ፣ አዲስ ተስፋ ፤
ብሩህ አለም ፣ ከ ሰማይ የሰፋ ፤
ተሰጥቶኛል ከላይ !
የ እግዜር እጅ አለበት ፣ ሁሌም ዕድሌ ላይ ።
አንቺ የማህሌት እጣን ፣
የ እየሩሳሌም ጠበል ፤
አንቺን እንዲሰጠኝ ፣
በምን ቋንቋ ልሳል ? ፣
ስለማንትስ ልበል ? ፤
የት ደብር ልሳልሽ? ፣ የት ገዳም ልመንን ፤
ህልሜ እኝዲሆን እውን ፤
አዲስ ህይወት ፣ አዲስ ተስፋ ፤
ብሩህ አለም ፣ ከ ሰማይ የሰፋ ፤
ተሰጥቶኛል ከላይ !
የ እግዜር እጅ አለበት ፣ ሁሌም ዕድሌ ላይ ።
ብሳልሽ ባስስሽ ፣ ቢጠቁርልሽ መልኬ ፤
ከፈጠረኝ ውጪ ፣ ማን ያቅና ልኬን ?
ትቆያለች እንጂ ፣ ፀሐይ ትወጣለች ፤
አንቺ ያለሽባት ፣
ጨልሞ አይቀረም ፤ ነገ ትመጣለች ፤
ታምኜ ለህልሜ !
ነገን ሄጄ ባያት ፤ በ ምናብ ተልኬ ፤
አዲስ ህይወት አየሁ ፣ ልክሽ ሆኖ ልኬ።
አዲስ ህይወት ፣ አዲስ ተስፋ ፤
ብሩህ አለም ፣ ከ ሰማይ የሰፋ ፤
ተሰጥቶኛል ከላይ !
የ እግዜር እጅ አለበት ፣ ሁሌም ዕድሌ ላይ ።