ማ.....ህሌትሽ
ከሰማየ ሰማይ ..ከእዮር ከራማ
በዳዊትሽ ፀሎት ብሌን እና ሻማ
አደምጣለሁ ..ፀሎት ውብ የያሬድ ዜማ
.
ከማህተብሽ ማዶ አይኔ እያማተረ
ዲያቆኑ ስገዱ ሲል እግሬ ቆሞ ቀረ
አርምሞ በዝቶብኝ
በነጠላሽ ስርሀት ዶግማና ትሁፊት
ካህኑ አሀዱ ሲል እኔ እላለው ስብሀት
.
በዘመን ከምሞት የኔ የኔ እያልኩሽ
መሽቶ ስለማይቀር ልቁም ማህሌትሽ
- ነፍሴ ስ..ለ...ም..ታ..ፈ...ቅ...ር....ሽ